- አማርኛ
- English
አዋሳ የተመሰረተቸው በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1952 ዓመተ ምሕረት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በፍጥነት እያደጉ ካሉት ከተማዎች ውስጥ አንዷ ናት። አዋሳ በዋናው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ፣ በአዋሳ ሐይቅ ምሥራቃዊ ዳርቻ፣ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ፣ 275 ኪሜ (171 ማይል) ርቀት ላይ የምትገኝ ውብ ከተማ ናት።
በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1960ዎቹ መግቢያ ላይ፣ አዋሳ፣ ይርጋ ዓለምን በመተካት፣ የቀድሞው የሲዳማ ክፍለ ሀገር ዋና ከተማ ሆነች። በደርግ ዘመን፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1970ዎቹ መግቢያ ላይ፣ አዋሳ የደቡባዊ (የአርሲ፣ የባሌ፣ የጋሞ ጎፋ እና የሲዳማ) አስተዳደር ማዕከል በመሆን አገለገለች። በአሁኑ ወቅት፣ አዋሳ የደቡብ ክልል እና የሲዳማ ዞን ዋና ከተማ ናት።
የቅርብ ጊዜ የከተማ አስተያየቶች፥